top of page
1000019813.jpg

በሞንትጎመሪ ካውንቲ (Montgomery County) ውስጥ እርዳታ ለሚሹ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች ህይወት ቀያሪ የሆኑ እድሎችን መፍጠር።

ሁሉም ፕሮግራሞች ያለምንም ክፍያ በነፃየሚሰጡ ናቸው። የሁሉም ደንበኞች መረጃ ሙሉ በሙሉ በሚስጥር የተጠበቀ ነው።

አይደንቲቲ ሰዎች በሚፈልጉን ጊዜ እና ቦታ ሁሉ አብሯቸው ይገኛል። በትምህርት ቤቶች፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ወይም በስፖርት ሜዳዎች፤ ወጣቶች እና ቤተሰቦች ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጓቸውን ማህበራዊ-ስሜታዊ፣ የትምህርት፣ የሥራ እና የህይወት ክህሎቶችን እንመክራለን፣ እናስተምራለን።

አይደንቲቲ በየዓመቱ ለ10,000 ወጣቶች እና ቤተሰቦች አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ከፍተኛ እርዳታ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች የሚኖሩ 50,000 ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። 

02.09.2026-HTES Students raising hands for SEL participation.jpeg
“አይደንቲቲ በእኔ አመነብኝ፣ እኔም በራሴ እንድተማመን አስተማረኝ።”
 ~ሊዲሴ (Lidice)፣ ዕድሜ 17

እርዳታ ለሚሹ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚሰጥ የክስ መዝገብ አያያዝ (Case Management) አገልግሎት

  • የስሜት ድጋፍ ሰጪ ቡድኖች እና የምክር አገልግሎት

  • እንግሊዘኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ማስተማር [English as a Second Language (ESL)]

  • ቤተሰብን የሚያጠናክሩ የቡድን ውይይቶች

  • በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋዎች የሚሰጥ የGED (የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና) ዝግጅት (ዕድሜያቸው ከ16-25 ለሆኑ)

  • የህይወት ዘመን ክህሎት ስልጠና (ለወጣቶች)

  • የወላጆች ትምህርት እና የተሳትፎ ወርክሾፖች

  • የሱስ እፆች መከላከል እና ጣልቃ ገብነት (ዕድሜያቸው ከ10-25 ለሆኑ)

  • የህክምና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ሰጪ ሞግዚትነት (የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዕድሜ ላላቸው)

  • የሙያ እና የሥራ ምክር፣ ስልጠና፣ የሥራ ፍለጋ ማማከር እና የሥራ ቅጥርን የሚያካትት የሰራተኛ ሃይል ልማት

  • የወጣቶች እድል ማዕከላት (ዕድሜያቸው ከ14-25 ለሆኑ)

 በተመረጡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • በንባብ እና በSTEM (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ) ትምህርቶች አካዳሚያዊ ድጋፍ እና ማበልፀጊያ

  • ድልድይ ወደ ጤናማነት / Bridge to Wellness (በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የተመሰረተ)

  • የቤተሰብ የክስ መዝገብ አያያዝ/ኬዝ ማኔጅመንት

  • የወላጅ ትምህርት

  • በጎ የወጣቶች እድገት (Positive Youth Development)

  • የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች

  • ማህበራዊ እና ስሜታዊ ድጋፍ እንዲሁም የክህሎት ግንባታ

  • የህክምና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ሰጪ ሞግዚትነት

  • የጤና ማዕከላት (በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የተመሰረተ)

ES Final two teams_edited_edited.jpg

የምናምንበት እሴቶች፦

  • እያንዳንዱ ልጅ አቅም አለው።

  • ወጣቶች ከአንድ በላይ እድል ይገባቸዋል።

  • የጎለበቱ ቤተሰቦች እና ጠንካራ የድጋፍ ስርዓቶች አስፈላጊ ናቸው።

  • ደንበኞች የቋንቋ፣ የባህል እና የማህበረሰብ ግንኙነታቸው ከግምት ውስጥ የሚያስገባ አገልግሎት ይደርሳቸዋል።

  • ሞንትጎመሪ ካውንቲ የበለጠ ጠንካራ የሚሆነው እያንዳንዱ ሰው ሲከበር እና ዋጋ ሲሰጠው ነው።

  • ሌሎችን ማገልገል እድል ነው፤ ከፍተኛ ጥራት እና ብቃትንም ይጠይቃል።

  

እንደ ቤተሰብ፣ እያንዳንዱን ስኬት እናከብራለን፣ ተጨማሪ እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜም ድጋፍ እንሰጣለን።

አገልግሎቶች በእንግሊዝኛ፣ ስፓኒሽ፣ ፈረንሳይኛ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲን ልዩ ልዩ ህዝቦች በሚወክሉ ሌሎች ቋንቋዎች ይገኛሉ። አይደንቲቲ ብዙ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰራተኞች አሉት። የእርስዎን ቋንቋ የሚናገር ሰራተኛ ከሌለ፣ የአስተርጓሚ አገልግሎት መጠቀም እንችላለን።

አገልግሎቶችን ለመጠየቅ

ለራስዎ ወይም ለሌላ ሰው አገልግሎት ለመጠየቅ፣ እባክዎን በድህረ ገፃችን ላይ ያለውን የሪፈራል (የአገልግሎት ጥያቄ) ፎርም ይሙሉ ወይም በስልክ ይደውሉልን።

የሪፈራል ፎርም

 

አገልግሎት ለመጠየቅ የመደወያ ስልክ ቁጥር፦ 301-800-5519
ለአጠቃላይ ጥያቄዎች፦ 301-963-5900 
ኢሜይል፦ info@identity-youth.org
ድረ ገጽ፦ www.Identity-youth.org

imagem.png

Entre em contato

Identidade, Inc.
415 East Diamond Ave.
Gaithersburg, MD 20877
Telefone: 301-963-5900

E-mail: Info@identity-youth.org

Receba atualizações

Assine nossa newsletter mensal para se manter informado.

Trabalhe Conosco

Candidate-se a uma vaga na Identity para ajudar a tornar o Condado de Montgomery um lugar melhor para todos os jovens e famílias.

Solicitar serviços

Para indicar você mesmo ou um cliente, use nosso formulário de indicação on-line abaixo ou ligue para 301-800-5519.

  • Facebook
  • Instagram
  • LinkedIn
  • YouTube

Copyright 2024 Identity, Inc. | Todos os direitos reservados

bottom of page